am_tw/bible/kt/god.md

1.4 KiB

እግዚአብሔር

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር አጽናፈ ዓለሙን ከምንም ያስገኘው ዘላለማዊ ፈጣሪን ያመለክታል። እግዚአብሔር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በሚባሉ ሦስት አካሎች ተገልጧል። የእግዚአብሔር ተፀውዖ (መጠሪያ) ስም፣ “ያህዌ” ነው።

  • እግዚአብሔር ሁሌም ነበረ፤ ምንም ነገር ከመሆኑ በፊት ነበረ፤ ለዘላለምም ይኖራል።
  • አጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ባለ ማንኛውም ነገር ሥልጣን ያለው እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው።
  • እግዚአብሔር ፍጹም ጻድቅ፣ እጅግ ጠበኛ፣ ቅዱስ፥ ኀጢአት የሌለበት፣ መልካም መሐሪና አፍቃሪ ነው።
  • እርሱ ኪዳን አክባሪ አምላክ ነው፤ እርሱ ተስፋ ቃሉን የሚፈጽም ነው።
  • ሰዎች የተፈጠሩት እርሱን ለማምለክ ነው፤ ማምለክ ያለባቸው እርሱን ብቻ ነው።
  • ስሙ፣ “ያህዌ” መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ይህም “እርሱ ነው” ወይም፣ “እኔ ነኝ” ወይም፣ “ሁሌም የምኖር” ማለት ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ሕላዌ ስለሌላቸውና ሰዎች በስሕተት ስለሚያመልኳቸው ስለ ሐሰተኛ አማልክትም ይናገራል።