am_tw/bible/kt/god.md

12 lines
1.4 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# እግዚአብሔር
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር አጽናፈ ዓለሙን ከምንም ያስገኘው ዘላለማዊ ፈጣሪን ያመለክታል። እግዚአብሔር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በሚባሉ ሦስት አካሎች ተገልጧል። የእግዚአብሔር ተፀውዖ (መጠሪያ) ስም፣ “ያህዌ” ነው።
* እግዚአብሔር ሁሌም ነበረ፤ ምንም ነገር ከመሆኑ በፊት ነበረ፤ ለዘላለምም ይኖራል።
* አጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ባለ ማንኛውም ነገር ሥልጣን ያለው እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው።
* እግዚአብሔር ፍጹም ጻድቅ፣ እጅግ ጠበኛ፣ ቅዱስ፥ ኀጢአት የሌለበት፣ መልካም መሐሪና አፍቃሪ ነው።
* እርሱ ኪዳን አክባሪ አምላክ ነው፤ እርሱ ተስፋ ቃሉን የሚፈጽም ነው።
* ሰዎች የተፈጠሩት እርሱን ለማምለክ ነው፤ ማምለክ ያለባቸው እርሱን ብቻ ነው።
* ስሙ፣ “ያህዌ” መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ይህም “እርሱ ነው” ወይም፣ “እኔ ነኝ” ወይም፣ “ሁሌም የምኖር” ማለት ነው።
* መጽሐፍ ቅዱስ ሕላዌ ስለሌላቸውና ሰዎች በስሕተት ስለሚያመልኳቸው ስለ ሐሰተኛ አማልክትም ይናገራል።