# እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር አጽናፈ ዓለሙን ከምንም ያስገኘው ዘላለማዊ ፈጣሪን ያመለክታል። እግዚአብሔር አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ በሚባሉ ሦስት አካሎች ተገልጧል። የእግዚአብሔር ተፀውዖ (መጠሪያ) ስም፣ “ያህዌ” ነው። * እግዚአብሔር ሁሌም ነበረ፤ ምንም ነገር ከመሆኑ በፊት ነበረ፤ ለዘላለምም ይኖራል። * አጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ባለ ማንኛውም ነገር ሥልጣን ያለው እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው። * እግዚአብሔር ፍጹም ጻድቅ፣ እጅግ ጠበኛ፣ ቅዱስ፥ ኀጢአት የሌለበት፣ መልካም መሐሪና አፍቃሪ ነው። * እርሱ ኪዳን አክባሪ አምላክ ነው፤ እርሱ ተስፋ ቃሉን የሚፈጽም ነው። * ሰዎች የተፈጠሩት እርሱን ለማምለክ ነው፤ ማምለክ ያለባቸው እርሱን ብቻ ነው። * ስሙ፣ “ያህዌ” መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሮአል፤ ይህም “እርሱ ነው” ወይም፣ “እኔ ነኝ” ወይም፣ “ሁሌም የምኖር” ማለት ነው። * መጽሐፍ ቅዱስ ሕላዌ ስለሌላቸውና ሰዎች በስሕተት ስለሚያመልኳቸው ስለ ሐሰተኛ አማልክትም ይናገራል።