am_tw/bible/kt/glory.md

9 lines
1.0 KiB
Markdown

# ክብር፣ የከበረ
በአጠቃላይ “ክብር” ማለት ምስጋና፣ ውበትና የላቀ ታላቅነት ማለት ነው። ክብር ያለው ነገር “የከበረ” ይባላል።
* አንዳንዴ “ክብር” ታልቅ ዋጋ እና አስፈላጊነት ያለውን ነገር ያመለክታል። በሌላ ዐውድ ደግሞ ውበትን፣ ድምቀትን ወይም ፍርድን ያመለክታል።
* ለምሳሌ፣ “የእረኞች ክብር” የሚለው ሐረግ በጎቻቸው የሚግጡት ሳር በብዛት ያለበትን ለምለም የግጦሽ ቦታ ያመለክታል።
* በተለይ ደግሞ ክብር በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ካለ ማንኛውም ሰውና ማንኛውም ነገር እጅግ የበለጠ ክቡር የሆነው እግዚአብሔርን ያመለክታል። ባሕርዩ ሁሉ ክብሩንና ውበቱን ይገልጻል።
* “መክበር” ማለት በአንድ ነገር መጓደድ ወይም መመካትን ያመለክታል።