# ክብር፣ የከበረ በአጠቃላይ “ክብር” ማለት ምስጋና፣ ውበትና የላቀ ታላቅነት ማለት ነው። ክብር ያለው ነገር “የከበረ” ይባላል። * አንዳንዴ “ክብር” ታልቅ ዋጋ እና አስፈላጊነት ያለውን ነገር ያመለክታል። በሌላ ዐውድ ደግሞ ውበትን፣ ድምቀትን ወይም ፍርድን ያመለክታል። * ለምሳሌ፣ “የእረኞች ክብር” የሚለው ሐረግ በጎቻቸው የሚግጡት ሳር በብዛት ያለበትን ለምለም የግጦሽ ቦታ ያመለክታል። * በተለይ ደግሞ ክብር በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ካለ ማንኛውም ሰውና ማንኛውም ነገር እጅግ የበለጠ ክቡር የሆነው እግዚአብሔርን ያመለክታል። ባሕርዩ ሁሉ ክብሩንና ውበቱን ይገልጻል። * “መክበር” ማለት በአንድ ነገር መጓደድ ወይም መመካትን ያመለክታል።