am_tw/bible/kt/glory.md

1.0 KiB

ክብር፣ የከበረ

በአጠቃላይ “ክብር” ማለት ምስጋና፣ ውበትና የላቀ ታላቅነት ማለት ነው። ክብር ያለው ነገር “የከበረ” ይባላል።

  • አንዳንዴ “ክብር” ታልቅ ዋጋ እና አስፈላጊነት ያለውን ነገር ያመለክታል። በሌላ ዐውድ ደግሞ ውበትን፣ ድምቀትን ወይም ፍርድን ያመለክታል።
  • ለምሳሌ፣ “የእረኞች ክብር” የሚለው ሐረግ በጎቻቸው የሚግጡት ሳር በብዛት ያለበትን ለምለም የግጦሽ ቦታ ያመለክታል።
  • በተለይ ደግሞ ክብር በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ካለ ማንኛውም ሰውና ማንኛውም ነገር እጅግ የበለጠ ክቡር የሆነው እግዚአብሔርን ያመለክታል። ባሕርዩ ሁሉ ክብሩንና ውበቱን ይገልጻል።
  • “መክበር” ማለት በአንድ ነገር መጓደድ ወይም መመካትን ያመለክታል።