am_tw/bible/kt/forgive.md

9 lines
920 B
Markdown

# ይቅር ማለት ይቅርታ
አንድን ሰው ይቅር ማለት ከዚህ ቀደም ባደረገው መጥፎ ነገር ቂም አለመያ ማለት ነው። “ይቅርታ” ሌላውን ይቅር የማለት ተግባር ነው።
* ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው ይቅር ማለት በፈጸመው ጥፋት እርሱን አለመቅጣት ማለት ነው።
* ቃሉ “ዕዳ መሰረዙን” በሚያመለክት መልኩ፣ “መሰረዝ” የሚል ትርጕም ባለው መልኩ ምሳሌያዊ አነጋገርም ይሆናል።
* ሰዎች ኀጢአታቸውን ሲናዘዙ ከኢየሱስ መስቀል ላይ መሥዋዕታዊ ሞት የተነሣ እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል።
* እርሱ ይቅር እንዳላቸው እነርሱም ሌሎችን ይቅር ማለት እንዳለባቸው ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አስተማረ።