am_tw/bible/kt/forgive.md

920 B

ይቅር ማለት ይቅርታ

አንድን ሰው ይቅር ማለት ከዚህ ቀደም ባደረገው መጥፎ ነገር ቂም አለመያ ማለት ነው። “ይቅርታ” ሌላውን ይቅር የማለት ተግባር ነው።

  • ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው ይቅር ማለት በፈጸመው ጥፋት እርሱን አለመቅጣት ማለት ነው።
  • ቃሉ “ዕዳ መሰረዙን” በሚያመለክት መልኩ፣ “መሰረዝ” የሚል ትርጕም ባለው መልኩ ምሳሌያዊ አነጋገርም ይሆናል።
  • ሰዎች ኀጢአታቸውን ሲናዘዙ ከኢየሱስ መስቀል ላይ መሥዋዕታዊ ሞት የተነሣ እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል።
  • እርሱ ይቅር እንዳላቸው እነርሱም ሌሎችን ይቅር ማለት እንዳለባቸው ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አስተማረ።