# ይቅር ማለት ይቅርታ አንድን ሰው ይቅር ማለት ከዚህ ቀደም ባደረገው መጥፎ ነገር ቂም አለመያ ማለት ነው። “ይቅርታ” ሌላውን ይቅር የማለት ተግባር ነው። * ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው ይቅር ማለት በፈጸመው ጥፋት እርሱን አለመቅጣት ማለት ነው። * ቃሉ “ዕዳ መሰረዙን” በሚያመለክት መልኩ፣ “መሰረዝ” የሚል ትርጕም ባለው መልኩ ምሳሌያዊ አነጋገርም ይሆናል። * ሰዎች ኀጢአታቸውን ሲናዘዙ ከኢየሱስ መስቀል ላይ መሥዋዕታዊ ሞት የተነሣ እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል። * እርሱ ይቅር እንዳላቸው እነርሱም ሌሎችን ይቅር ማለት እንዳለባቸው ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን አስተማረ።