am_tw/bible/kt/flesh.md

9 lines
953 B
Markdown

# ሥጋ
መጽሐፍ ቅዱስ ሥጋ ሲል ቃል በቃል የሰውን ወይም የእንስሳን ለስላሳውን የአካል ክፍል ያመለክታል።
* የሰው ልጆችን ወይም ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ሥጋ” የሚለውን በምሳሌያዊ አነጋገር ይጠቀምበታል።
* አዲስ ኪዳን፣ “ሥጋ” ኅጢአተኛውን የሰዎች ባሕርይ ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል።
* “የሥጋ ቁራጭ፣ የአጥንት ፍላጭ” የሚለው ፈሊጣዊ ቋንቋ በሥጋ የምንዛመደውን ሰው ማለት አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን፣ የልጅ ልጆችን፣ እኅት፣ ወንድሞችንና ሌሎችን የቅርብ ዘመዶችን ያመለክታል።
* “ሥጋና ደም” የአንድ ሰው የቀደሙ አባቶችንና እናቶችንም ያመለክታል።