# ሥጋ መጽሐፍ ቅዱስ ሥጋ ሲል ቃል በቃል የሰውን ወይም የእንስሳን ለስላሳውን የአካል ክፍል ያመለክታል። * የሰው ልጆችን ወይም ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ሥጋ” የሚለውን በምሳሌያዊ አነጋገር ይጠቀምበታል። * አዲስ ኪዳን፣ “ሥጋ” ኅጢአተኛውን የሰዎች ባሕርይ ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል። * “የሥጋ ቁራጭ፣ የአጥንት ፍላጭ” የሚለው ፈሊጣዊ ቋንቋ በሥጋ የምንዛመደውን ሰው ማለት አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን፣ የልጅ ልጆችን፣ እኅት፣ ወንድሞችንና ሌሎችን የቅርብ ዘመዶችን ያመለክታል። * “ሥጋና ደም” የአንድ ሰው የቀደሙ አባቶችንና እናቶችንም ያመለክታል።