am_tw/bible/kt/flesh.md

953 B

ሥጋ

መጽሐፍ ቅዱስ ሥጋ ሲል ቃል በቃል የሰውን ወይም የእንስሳን ለስላሳውን የአካል ክፍል ያመለክታል።

  • የሰው ልጆችን ወይም ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ለማመልከት መጽሐፍ ቅዱስ፣ “ሥጋ” የሚለውን በምሳሌያዊ አነጋገር ይጠቀምበታል።
  • አዲስ ኪዳን፣ “ሥጋ” ኅጢአተኛውን የሰዎች ባሕርይ ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል።
  • “የሥጋ ቁራጭ፣ የአጥንት ፍላጭ” የሚለው ፈሊጣዊ ቋንቋ በሥጋ የምንዛመደውን ሰው ማለት አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን፣ የልጅ ልጆችን፣ እኅት፣ ወንድሞችንና ሌሎችን የቅርብ ዘመዶችን ያመለክታል።
  • “ሥጋና ደም” የአንድ ሰው የቀደሙ አባቶችንና እናቶችንም ያመለክታል።