am_tw/bible/kt/falsegod.md

11 lines
1.3 KiB
Markdown

# ሐሰተኛ አምላክ፣ ባዕድ አምላክ፣ ጣዖት
ሐሰተኛ አምላክ በአንዱ እውነተኛ አምላክ ቦታ ሰዎች የሚያመልኩት ነገር ነው። ወንድ ጣዖት እንዳለ ሁሉ ሴት ጥዖትም አለች።
* ሐሰተኛ አማልክት ሕልውና የላቸውም፤ እውነተኛ አምላክ ያህዌ ብቻ ነው።
* አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ነገሮች ሐሰተኛ አማልክቶቻቸውን የሚወክልላቸው ምስል ይሠራሉ።
* ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው የእግዚአብሔር ሕዝብ ሐሰተኛ አማልክት ለማምለክ በተደጋጋሚ ለእርሱ ከመታዘዝ ወደኋላ ሄደው እንደነበር እናያለን።
* የሚያመልኳቸው ሐሰተኛ አማልክትና ጣዖቶች ኅይል እንዳላቸው እንዲያምኑ ብዙውን ጊዜ አጋንንት ሰዎችን ያሳስታሉ።
* በኣል፣ ዳጎንና ሞሎክ መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሰዎች ያመልኳቸው ከነበሩ ብዙ ሐሰተኛ አማልክት መከከል ሦስቱ ናቸው።
* አሼራና አርጤምስ(ዳያና) የጥንት ሰዎች ያመልኳቸው ከነበሩ ሴት አማልክት ሁለቱ ነበሩ።