am_tw/bible/kt/falsegod.md

1.3 KiB

ሐሰተኛ አምላክ፣ ባዕድ አምላክ፣ ጣዖት

ሐሰተኛ አምላክ በአንዱ እውነተኛ አምላክ ቦታ ሰዎች የሚያመልኩት ነገር ነው። ወንድ ጣዖት እንዳለ ሁሉ ሴት ጥዖትም አለች።

  • ሐሰተኛ አማልክት ሕልውና የላቸውም፤ እውነተኛ አምላክ ያህዌ ብቻ ነው።
  • አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ነገሮች ሐሰተኛ አማልክቶቻቸውን የሚወክልላቸው ምስል ይሠራሉ።
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው የእግዚአብሔር ሕዝብ ሐሰተኛ አማልክት ለማምለክ በተደጋጋሚ ለእርሱ ከመታዘዝ ወደኋላ ሄደው እንደነበር እናያለን።
  • የሚያመልኳቸው ሐሰተኛ አማልክትና ጣዖቶች ኅይል እንዳላቸው እንዲያምኑ ብዙውን ጊዜ አጋንንት ሰዎችን ያሳስታሉ።
  • በኣል፣ ዳጎንና ሞሎክ መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሰዎች ያመልኳቸው ከነበሩ ብዙ ሐሰተኛ አማልክት መከከል ሦስቱ ናቸው።
  • አሼራና አርጤምስ(ዳያና) የጥንት ሰዎች ያመልኳቸው ከነበሩ ሴት አማልክት ሁለቱ ነበሩ።