# ሐሰተኛ አምላክ፣ ባዕድ አምላክ፣ ጣዖት ሐሰተኛ አምላክ በአንዱ እውነተኛ አምላክ ቦታ ሰዎች የሚያመልኩት ነገር ነው። ወንድ ጣዖት እንዳለ ሁሉ ሴት ጥዖትም አለች። * ሐሰተኛ አማልክት ሕልውና የላቸውም፤ እውነተኛ አምላክ ያህዌ ብቻ ነው። * አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ነገሮች ሐሰተኛ አማልክቶቻቸውን የሚወክልላቸው ምስል ይሠራሉ። * ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው የእግዚአብሔር ሕዝብ ሐሰተኛ አማልክት ለማምለክ በተደጋጋሚ ለእርሱ ከመታዘዝ ወደኋላ ሄደው እንደነበር እናያለን። * የሚያመልኳቸው ሐሰተኛ አማልክትና ጣዖቶች ኅይል እንዳላቸው እንዲያምኑ ብዙውን ጊዜ አጋንንት ሰዎችን ያሳስታሉ። * በኣል፣ ዳጎንና ሞሎክ መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ሰዎች ያመልኳቸው ከነበሩ ብዙ ሐሰተኛ አማልክት መከከል ሦስቱ ናቸው። * አሼራና አርጤምስ(ዳያና) የጥንት ሰዎች ያመልኳቸው ከነበሩ ሴት አማልክት ሁለቱ ነበሩ።