am_tw/bible/kt/evil.md

904 B

ክፉ፣ ዐመጽ(ዐመጸኛ)፣ ዐመጻ

“ክፉ” እና “ዐመጸኛ” የተሰኙት ቃሎች ሁለቱም የእግዚአብሔርን ቅዱስ ባሕርይና ፈቃድ የሚቃወም ማንኛውንም ነገር ያመለክታሉ።

  • “ክፉ” የሚለው ቃል የሰውን ፀባይ የሚያመለክት ሲሆን፣ “ዐመጸኛ” የሚለው ደግሞ የሰውን ባሕርይ ሊያመለክት ይችላል። ይሁን እንጂ፣ የሁለቱም ትርጉም ተመሳሳይ ነው።
  • “ዐመጻ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ዐመጽ ሲያደርጉ የሚኖረውን ሁኔታ ነው።
  • ሰዎች ሌሎችን በመግደል፣ በመስረቅ፣ ስም በማጥፋት ወይም በሚፈጽሙት የጭካኔ ተግባር የክፋትን ወይም የዐመጻን ውጤት በግልጽ ማየት ይቻላል።