am_tw/bible/kt/evil.md

8 lines
904 B
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ክፉ፣ ዐመጽ(ዐመጸኛ)፣ ዐመጻ
“ክፉ” እና “ዐመጸኛ” የተሰኙት ቃሎች ሁለቱም የእግዚአብሔርን ቅዱስ ባሕርይና ፈቃድ የሚቃወም ማንኛውንም ነገር ያመለክታሉ።
* “ክፉ” የሚለው ቃል የሰውን ፀባይ የሚያመለክት ሲሆን፣ “ዐመጸኛ” የሚለው ደግሞ የሰውን ባሕርይ ሊያመለክት ይችላል። ይሁን እንጂ፣ የሁለቱም ትርጉም ተመሳሳይ ነው።
* “ዐመጻ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ዐመጽ ሲያደርጉ የሚኖረውን ሁኔታ ነው።
* ሰዎች ሌሎችን በመግደል፣ በመስረቅ፣ ስም በማጥፋት ወይም በሚፈጽሙት የጭካኔ ተግባር የክፋትን ወይም የዐመጻን ውጤት በግልጽ ማየት ይቻላል።