# ክፉ፣ ዐመጽ(ዐመጸኛ)፣ ዐመጻ “ክፉ” እና “ዐመጸኛ” የተሰኙት ቃሎች ሁለቱም የእግዚአብሔርን ቅዱስ ባሕርይና ፈቃድ የሚቃወም ማንኛውንም ነገር ያመለክታሉ። * “ክፉ” የሚለው ቃል የሰውን ፀባይ የሚያመለክት ሲሆን፣ “ዐመጸኛ” የሚለው ደግሞ የሰውን ባሕርይ ሊያመለክት ይችላል። ይሁን እንጂ፣ የሁለቱም ትርጉም ተመሳሳይ ነው። * “ዐመጻ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰዎች ዐመጽ ሲያደርጉ የሚኖረውን ሁኔታ ነው። * ሰዎች ሌሎችን በመግደል፣ በመስረቅ፣ ስም በማጥፋት ወይም በሚፈጽሙት የጭካኔ ተግባር የክፋትን ወይም የዐመጻን ውጤት በግልጽ ማየት ይቻላል።