am_tw/bible/kt/eunuch.md

1.1 KiB

ጃንደረባ

ብዙ ጊዜ፣ “ጃንደረባ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተኮላሸ ወንድን ነው በኋላ ግን ቃሉ አካላዊ ጉድለት ባይኖርባቸውም በአጠቃላይ ማንኛውንም የመንግሥት ባለሥልጣን የሚያመለክት ሆነ።

  • ብልታቸው በመጎዳቱ ወይም የግብረሥጋ ግንኙነት ማድረግ ባለመቻሉ፣ አንዳንዶች ጃንደረባ ሆነው እንደሚወለዱ ኢየሱስ ተናግሯል። አንዳንዶች ደግሞ በድንግልና እንደጃንደረባ መኖርን መርጠዋል።
  • በጥንት ዘመን ጃንደረቦች ብዙ ጊዜ የነገሥታቱን ሴቶች እንዲጠብቁ ቤተመንግሥት ውስጥ ያገለግሉ ነበር (ከነአስቴር ታሪክ መመልከት ይቻላል)
  • አንዳንድ ጃንደረቦች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ነበሩ፤ ይህን በአዲስ ኪዳን ከተጠቀሰው ፊልጶስ ወንጌል ከሰበከለት ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ማየት ይቻላል።