# ጃንደረባ ብዙ ጊዜ፣ “ጃንደረባ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተኮላሸ ወንድን ነው በኋላ ግን ቃሉ አካላዊ ጉድለት ባይኖርባቸውም በአጠቃላይ ማንኛውንም የመንግሥት ባለሥልጣን የሚያመለክት ሆነ። * ብልታቸው በመጎዳቱ ወይም የግብረሥጋ ግንኙነት ማድረግ ባለመቻሉ፣ አንዳንዶች ጃንደረባ ሆነው እንደሚወለዱ ኢየሱስ ተናግሯል። አንዳንዶች ደግሞ በድንግልና እንደጃንደረባ መኖርን መርጠዋል። * በጥንት ዘመን ጃንደረቦች ብዙ ጊዜ የነገሥታቱን ሴቶች እንዲጠብቁ ቤተመንግሥት ውስጥ ያገለግሉ ነበር (ከነአስቴር ታሪክ መመልከት ይቻላል) * አንዳንድ ጃንደረቦች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ነበሩ፤ ይህን በአዲስ ኪዳን ከተጠቀሰው ፊልጶስ ወንጌል ከሰበከለት ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ማየት ይቻላል።