am_tw/bible/kt/eunuch.md

8 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ጃንደረባ
ብዙ ጊዜ፣ “ጃንደረባ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የተኮላሸ ወንድን ነው በኋላ ግን ቃሉ አካላዊ ጉድለት ባይኖርባቸውም በአጠቃላይ ማንኛውንም የመንግሥት ባለሥልጣን የሚያመለክት ሆነ።
* ብልታቸው በመጎዳቱ ወይም የግብረሥጋ ግንኙነት ማድረግ ባለመቻሉ፣ አንዳንዶች ጃንደረባ ሆነው እንደሚወለዱ ኢየሱስ ተናግሯል። አንዳንዶች ደግሞ በድንግልና እንደጃንደረባ መኖርን መርጠዋል።
* በጥንት ዘመን ጃንደረቦች ብዙ ጊዜ የነገሥታቱን ሴቶች እንዲጠብቁ ቤተመንግሥት ውስጥ ያገለግሉ ነበር (ከነአስቴር ታሪክ መመልከት ይቻላል)
* አንዳንድ ጃንደረቦች ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖች ነበሩ፤ ይህን በአዲስ ኪዳን ከተጠቀሰው ፊልጶስ ወንጌል ከሰበከለት ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ማየት ይቻላል።