am_tw/bible/kt/eternity.md

1.1 KiB

ዘላለም፣ ዘላለማዊ

“ዘላለም” እና “ዘላለማዊ” በጣም ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን፣ የሚያመለክቱት ሁሌም የሚኖር ወይም ማለቂያ ማብቂያ የሌለውን ነገር ወይም ሁኔታ ነው።

  • “ዘላለም” ጅማሬም ሆነ ፍጻሜ የሌለውን ሁኔታ ያመለክታል። ማለቂያ፣ ማብቂያ የሌለው ሕይወትንም ያመለክታል።
  • ከዚህ የአሁን ሕይወት በኋላ የሰው ልጆች በመንግሥተ ሰማይ ከእግዚአብሔር ጋር ወይም ከእግዚአብሔር ተለይተው በገሃነም ዘላለምን ያሳልፋሉ።
  • ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም በመንግሥተ ሰማይ መኖርን ለማመልከት አዲስ ኪዳን ውስጥ “ዘላለማዊ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
  • “ከዘላለም እስከ ዘላለም” የሚለው ሐረግ ማለቂያ የሌለውን ጊዜ የሚያመለክት ሲሆን፣ ዘላለም ወይም የዘላለም ሕይወት ምን ማለት መሆኑን ይገልጻል።