# ዘላለም፣ ዘላለማዊ “ዘላለም” እና “ዘላለማዊ” በጣም ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን፣ የሚያመለክቱት ሁሌም የሚኖር ወይም ማለቂያ ማብቂያ የሌለውን ነገር ወይም ሁኔታ ነው። * “ዘላለም” ጅማሬም ሆነ ፍጻሜ የሌለውን ሁኔታ ያመለክታል። ማለቂያ፣ ማብቂያ የሌለው ሕይወትንም ያመለክታል። * ከዚህ የአሁን ሕይወት በኋላ የሰው ልጆች በመንግሥተ ሰማይ ከእግዚአብሔር ጋር ወይም ከእግዚአብሔር ተለይተው በገሃነም ዘላለምን ያሳልፋሉ። * ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም በመንግሥተ ሰማይ መኖርን ለማመልከት አዲስ ኪዳን ውስጥ “ዘላለማዊ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል። * “ከዘላለም እስከ ዘላለም” የሚለው ሐረግ ማለቂያ የሌለውን ጊዜ የሚያመለክት ሲሆን፣ ዘላለም ወይም የዘላለም ሕይወት ምን ማለት መሆኑን ይገልጻል።