am_tw/bible/kt/eternity.md

9 lines
1.1 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ዘላለም፣ ዘላለማዊ
“ዘላለም” እና “ዘላለማዊ” በጣም ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሲሆን፣ የሚያመለክቱት ሁሌም የሚኖር ወይም ማለቂያ ማብቂያ የሌለውን ነገር ወይም ሁኔታ ነው።
* “ዘላለም” ጅማሬም ሆነ ፍጻሜ የሌለውን ሁኔታ ያመለክታል። ማለቂያ፣ ማብቂያ የሌለው ሕይወትንም ያመለክታል።
* ከዚህ የአሁን ሕይወት በኋላ የሰው ልጆች በመንግሥተ ሰማይ ከእግዚአብሔር ጋር ወይም ከእግዚአብሔር ተለይተው በገሃነም ዘላለምን ያሳልፋሉ።
* ከእግዚአብሔር ጋር ለዘላለም በመንግሥተ ሰማይ መኖርን ለማመልከት አዲስ ኪዳን ውስጥ “ዘላለማዊ” የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
* “ከዘላለም እስከ ዘላለም” የሚለው ሐረግ ማለቂያ የሌለውን ጊዜ የሚያመለክት ሲሆን፣ ዘላለም ወይም የዘላለም ሕይወት ምን ማለት መሆኑን ይገልጻል።