am_tw/bible/kt/ephod.md

9 lines
1.1 KiB
Markdown

# ኤፉድ
ኤፉድ እስራኤላውያን ካህናት ይለብሱት የነበረ መጎናጸፊያ ዐይነት ጨርቅ ነው። ትከሻ ላይ የሚገናኙ የፊትና የኋላ የሚባሉ ሁለት ክፍሎች ነበሩት፤ ከዚያም በጨርቅ መታጠቂያ ወገብ ላይ ይታሰር ነበር።
* አንዱ አይነት ኤፉድ ከተራ ተልባ እግር የሚሠራ ሲሆን፣ የሚለብሱትም ተራ ካህናት ነበሩ።
* ሊቀ ካህኑ የሚለብሰው ኤፉድ በወርቅ ያጌጠና በሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ጥልፍ የተሠራ ነበር።
* የሊቀ ካህኑ ደረት ልብስ ከኤፉዱ ፉት ለፊት አካል ጋር ይያያዛል፣ ከደረት ልብሱ በስተጀርባ አንድን ጉዳይ አመልክቶ የእርሱ ፈቃድ ምን እንደሆነ የሚጠይቅባቸው የከበሩ ድንጋዮች ኡሪምና ቱሚም ይቀመጣሉ።
* መሳፍንቱ ጌዴዎን በስሕተት ከወርቅ የሠራውን ኤፉድ እስራኤላውያን እንደ ጣዖት ሲያመልኩት ነበር።