# ኤፉድ ኤፉድ እስራኤላውያን ካህናት ይለብሱት የነበረ መጎናጸፊያ ዐይነት ጨርቅ ነው። ትከሻ ላይ የሚገናኙ የፊትና የኋላ የሚባሉ ሁለት ክፍሎች ነበሩት፤ ከዚያም በጨርቅ መታጠቂያ ወገብ ላይ ይታሰር ነበር። * አንዱ አይነት ኤፉድ ከተራ ተልባ እግር የሚሠራ ሲሆን፣ የሚለብሱትም ተራ ካህናት ነበሩ። * ሊቀ ካህኑ የሚለብሰው ኤፉድ በወርቅ ያጌጠና በሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ጥልፍ የተሠራ ነበር። * የሊቀ ካህኑ ደረት ልብስ ከኤፉዱ ፉት ለፊት አካል ጋር ይያያዛል፣ ከደረት ልብሱ በስተጀርባ አንድን ጉዳይ አመልክቶ የእርሱ ፈቃድ ምን እንደሆነ የሚጠይቅባቸው የከበሩ ድንጋዮች ኡሪምና ቱሚም ይቀመጣሉ። * መሳፍንቱ ጌዴዎን በስሕተት ከወርቅ የሠራውን ኤፉድ እስራኤላውያን እንደ ጣዖት ሲያመልኩት ነበር።