am_tw/bible/kt/ephod.md

1.1 KiB

ኤፉድ

ኤፉድ እስራኤላውያን ካህናት ይለብሱት የነበረ መጎናጸፊያ ዐይነት ጨርቅ ነው። ትከሻ ላይ የሚገናኙ የፊትና የኋላ የሚባሉ ሁለት ክፍሎች ነበሩት፤ ከዚያም በጨርቅ መታጠቂያ ወገብ ላይ ይታሰር ነበር።

  • አንዱ አይነት ኤፉድ ከተራ ተልባ እግር የሚሠራ ሲሆን፣ የሚለብሱትም ተራ ካህናት ነበሩ።
  • ሊቀ ካህኑ የሚለብሰው ኤፉድ በወርቅ ያጌጠና በሰማያዊ፣ ሐምራዊና ቀይ ጥልፍ የተሠራ ነበር።
  • የሊቀ ካህኑ ደረት ልብስ ከኤፉዱ ፉት ለፊት አካል ጋር ይያያዛል፣ ከደረት ልብሱ በስተጀርባ አንድን ጉዳይ አመልክቶ የእርሱ ፈቃድ ምን እንደሆነ የሚጠይቅባቸው የከበሩ ድንጋዮች ኡሪምና ቱሚም ይቀመጣሉ።
  • መሳፍንቱ ጌዴዎን በስሕተት ከወርቅ የሠራውን ኤፉድ እስራኤላውያን እንደ ጣዖት ሲያመልኩት ነበር።