am_tw/bible/kt/discipline.md

8 lines
940 B
Markdown

# ሥርዓት፥ ራስን መግዛት ወይም ራስን በሥርዓት መምራት
“ሥርዓት” ለተወሰኑ ግብረ ገባዊ መመሪያዎች እንዲታዘዙ ሰዎችን መሠልጠንን ነው የሚያመለክተው።
* ግብረ ገባዊ መመሪያዎችንና አቅጣጫዎችን በመስጠትና እንዲታዘዙ በማስተማር ወላጆች ልጆቻቸውን ሥርዓት ያስይዛሉ።
* በተመሳሳይ መንገድ ጤናማ መንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖራቸውና እንደ ደስታ፣ ትዕግሥትን የመሳሰሉ ፍሬዎች እንዲያፈሩ እግዚአብሔርም ልጆቹን ሥርዓት ያስይዛል።
* ሥርዓት ሲባል እግዚአብሔርን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚቻል መመሪያን እንደሚያመለክት ሁሉ፣ ከእርሱ ፈቀድ ውጪ የሆኑትን መቅጣትንም ያካትታል።