am_tw/bible/kt/discipline.md

940 B

ሥርዓት፥ ራስን መግዛት ወይም ራስን በሥርዓት መምራት

“ሥርዓት” ለተወሰኑ ግብረ ገባዊ መመሪያዎች እንዲታዘዙ ሰዎችን መሠልጠንን ነው የሚያመለክተው።

  • ግብረ ገባዊ መመሪያዎችንና አቅጣጫዎችን በመስጠትና እንዲታዘዙ በማስተማር ወላጆች ልጆቻቸውን ሥርዓት ያስይዛሉ።
  • በተመሳሳይ መንገድ ጤናማ መንፈሳዊ ሕይወት እንዲኖራቸውና እንደ ደስታ፣ ትዕግሥትን የመሳሰሉ ፍሬዎች እንዲያፈሩ እግዚአብሔርም ልጆቹን ሥርዓት ያስይዛል።
  • ሥርዓት ሲባል እግዚአብሔርን እንዴት ደስ ማሰኘት እንደሚቻል መመሪያን እንደሚያመለክት ሁሉ፣ ከእርሱ ፈቀድ ውጪ የሆኑትን መቅጣትንም ያካትታል።