am_tw/bible/kt/disciple.md

1.4 KiB

ደቀ መዝሙር

“ደቀ መዝሙር” በቃልም ሆነ በሕይወት ምሳሌነት ከመምህሩ ለመማር ሲል ብዙ ጊዜውን ከመምህሩ ጋር የሚያሳልፍ ሰው ነው።

  • ትምህርቱን በመስማትና ለእርሱ በመታዘዝ በየሄደበት ሁሉ ኢየሱስን የሚከተሉ ሰዎች፣ “ደቀ መዛሙርት” ይባላሉ።
  • መጥምቁ ዮሐንስም የራሱ ደቀ መዛሙርት ነበሩት።
  • ኢየሱስ በዚህ ምድር ባገለገለበት ዘመን እርሱን የተከተለና ትምህርቶቹን ያደመጡ ብዙ ደቀ መዛሙርት ነበሩት።
  • የቅርብ ተከታዮቹ እንዲሆኑ ኢየሱስ አሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት መረጠ፤ እነዚህም የእርሱ “ሐዋርያት” የተባሉት ናቸው።
  • አሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት፣ “ደቀ መዛሙርት” ወይም፣ “አሥራ ሁለቱ” በሚል ስያሜ መጠራታቸው ቀጥሎአል።
  • ወደ ሰማይ ከመሄዱ ጥቂት ቀደም ሲል የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ሌሎች ሰዎችን እንዲያስተምሩ ኢየሱስ ደቀ መዝሙርቱን አዝዞአል።
  • በኢየሱስ የሚያምንና ለእርሱ ትምህርት የሚታዘዝ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ይባላል።