12 lines
1.4 KiB
Markdown
12 lines
1.4 KiB
Markdown
|
# ደቀ መዝሙር
|
||
|
|
||
|
“ደቀ መዝሙር” በቃልም ሆነ በሕይወት ምሳሌነት ከመምህሩ ለመማር ሲል ብዙ ጊዜውን ከመምህሩ ጋር የሚያሳልፍ ሰው ነው።
|
||
|
|
||
|
* ትምህርቱን በመስማትና ለእርሱ በመታዘዝ በየሄደበት ሁሉ ኢየሱስን የሚከተሉ ሰዎች፣ “ደቀ መዛሙርት” ይባላሉ።
|
||
|
* መጥምቁ ዮሐንስም የራሱ ደቀ መዛሙርት ነበሩት።
|
||
|
* ኢየሱስ በዚህ ምድር ባገለገለበት ዘመን እርሱን የተከተለና ትምህርቶቹን ያደመጡ ብዙ ደቀ መዛሙርት ነበሩት።
|
||
|
* የቅርብ ተከታዮቹ እንዲሆኑ ኢየሱስ አሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት መረጠ፤ እነዚህም የእርሱ “ሐዋርያት” የተባሉት ናቸው።
|
||
|
* አሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት፣ “ደቀ መዛሙርት” ወይም፣ “አሥራ ሁለቱ” በሚል ስያሜ መጠራታቸው ቀጥሎአል።
|
||
|
* ወደ ሰማይ ከመሄዱ ጥቂት ቀደም ሲል የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ሌሎች ሰዎችን እንዲያስተምሩ ኢየሱስ ደቀ መዝሙርቱን አዝዞአል።
|
||
|
* በኢየሱስ የሚያምንና ለእርሱ ትምህርት የሚታዘዝ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ይባላል።
|