# ደቀ መዝሙር “ደቀ መዝሙር” በቃልም ሆነ በሕይወት ምሳሌነት ከመምህሩ ለመማር ሲል ብዙ ጊዜውን ከመምህሩ ጋር የሚያሳልፍ ሰው ነው። * ትምህርቱን በመስማትና ለእርሱ በመታዘዝ በየሄደበት ሁሉ ኢየሱስን የሚከተሉ ሰዎች፣ “ደቀ መዛሙርት” ይባላሉ። * መጥምቁ ዮሐንስም የራሱ ደቀ መዛሙርት ነበሩት። * ኢየሱስ በዚህ ምድር ባገለገለበት ዘመን እርሱን የተከተለና ትምህርቶቹን ያደመጡ ብዙ ደቀ መዛሙርት ነበሩት። * የቅርብ ተከታዮቹ እንዲሆኑ ኢየሱስ አሥራ ሁለት ደቀ መዛሙርት መረጠ፤ እነዚህም የእርሱ “ሐዋርያት” የተባሉት ናቸው። * አሥራ ሁለቱ የኢየሱስ ሐዋርያት፣ “ደቀ መዛሙርት” ወይም፣ “አሥራ ሁለቱ” በሚል ስያሜ መጠራታቸው ቀጥሎአል። * ወደ ሰማይ ከመሄዱ ጥቂት ቀደም ሲል የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ ሌሎች ሰዎችን እንዲያስተምሩ ኢየሱስ ደቀ መዝሙርቱን አዝዞአል። * በኢየሱስ የሚያምንና ለእርሱ ትምህርት የሚታዘዝ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ይባላል።