am_tw/bible/kt/demon.md

1.2 KiB

ጋኔን፣ ክፉ መንፈስ፣ ርኵሳን መናፍስት

እነዚህ ሁሉ የሚያመለክቱት አጋንንትን ሲሆን፣ አጋንንት የእግዚአብሔርን ፈቀድ የሚቀወሙ መንፈሳዊ ፍጥረቶች ናቸው።

  • እርሱን እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር መላእክትን ፈጠረ። ዲያብሎስ በእግዚአብሔር ላይ ሲያምጽ ከመላእክቱም ጥቂቶቹ በማመጻቸው ከሰማይ ተጣሉ። አጋንንትና ክፉ መናፍስት፣ “እነዚህ የተጣሉ” መላእክት እንደ ሆኑ ይታሰባል።
  • እነዚህ አጋንንት አንዳንዴ፣ “ርኵሳን መናፍስት” ተብለው ይጠራሉ። “ርኵስ” “ንጹሕ ያልሆነ” ወይም፣ “ክፉ” ወይም፣ “ቅዱስ ያልሆነ” ማለት ነው።
  • አጋንንት የሚያገለግሉት ዲያብሎስን ስለ ሆነ ክፉ ነገር ያደርጋሉ። አንዳንድ ጊዜ እነርሱ ውስጥ በመግባት ሰዎችን ይቆጣጠራሉ።
  • አጋንንት ከሰው የበለጠ ብርቱ ቢሆኑም፣ የእግዚአብሔርን ያህል ግን ብርቱ አይደሉም።