# ጋኔን፣ ክፉ መንፈስ፣ ርኵሳን መናፍስት እነዚህ ሁሉ የሚያመለክቱት አጋንንትን ሲሆን፣ አጋንንት የእግዚአብሔርን ፈቀድ የሚቀወሙ መንፈሳዊ ፍጥረቶች ናቸው። * እርሱን እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር መላእክትን ፈጠረ። ዲያብሎስ በእግዚአብሔር ላይ ሲያምጽ ከመላእክቱም ጥቂቶቹ በማመጻቸው ከሰማይ ተጣሉ። አጋንንትና ክፉ መናፍስት፣ “እነዚህ የተጣሉ” መላእክት እንደ ሆኑ ይታሰባል። * እነዚህ አጋንንት አንዳንዴ፣ “ርኵሳን መናፍስት” ተብለው ይጠራሉ። “ርኵስ” “ንጹሕ ያልሆነ” ወይም፣ “ክፉ” ወይም፣ “ቅዱስ ያልሆነ” ማለት ነው። * አጋንንት የሚያገለግሉት ዲያብሎስን ስለ ሆነ ክፉ ነገር ያደርጋሉ። አንዳንድ ጊዜ እነርሱ ውስጥ በመግባት ሰዎችን ይቆጣጠራሉ። * አጋንንት ከሰው የበለጠ ብርቱ ቢሆኑም፣ የእግዚአብሔርን ያህል ግን ብርቱ አይደሉም።