am_tw/bible/kt/deacon.md

1.2 KiB

ዲያቆን

ዲያቆን ምግብን ወይም ገንዘብን በመሳሰሉ ተግባራዊ ነገሮች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን በመርዳት የሚያገለግል ሰው ነው።

  • “ዲያቆን” የሚለው ቃል በቀጥታ የተወሰደው “ባርያ” ወይም “አገልጋይ” የሚል ትርጕም ካለው ግሪክ ቃል ነው።
  • የጥንት ክርስቲያኖች ከነበሩበት ዘመን ጀምሮ ዲያቆን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነኛ ድርሻ ያለው የአገልግሎት ዘርፍ ነው።
  • ለምሳሌ ከአዲስ ኪዳን እንደምንመለከተው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላሉ መበለቶችና ድኾች ገንዘብና ምግብ በአግባቡ መዳረሱን የሚያጣሩ ዲያቆናት ነበሩ።
  • “ዲያቆን” የተሰኘው ቃል፣ “የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ” ወይም፣ “የቤተ ክርስቲያን ሠራተኛ” ተብሎ ሊተረጎም ወይም የአጥቢያው ክርስቲያን ማኅበረ ሰብን የሚጠቅም ተግባር እንዲፈጽም በሥርዐት መሾምን በሚያሳይ ሌላ ሐረግ ወይም ቃል መጠቀም ይችላል።