# ዲያቆን ዲያቆን ምግብን ወይም ገንዘብን በመሳሰሉ ተግባራዊ ነገሮች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን በመርዳት የሚያገለግል ሰው ነው። * “ዲያቆን” የሚለው ቃል በቀጥታ የተወሰደው “ባርያ” ወይም “አገልጋይ” የሚል ትርጕም ካለው ግሪክ ቃል ነው። * የጥንት ክርስቲያኖች ከነበሩበት ዘመን ጀምሮ ዲያቆን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነኛ ድርሻ ያለው የአገልግሎት ዘርፍ ነው። * ለምሳሌ ከአዲስ ኪዳን እንደምንመለከተው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላሉ መበለቶችና ድኾች ገንዘብና ምግብ በአግባቡ መዳረሱን የሚያጣሩ ዲያቆናት ነበሩ። * “ዲያቆን” የተሰኘው ቃል፣ “የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ” ወይም፣ “የቤተ ክርስቲያን ሠራተኛ” ተብሎ ሊተረጎም ወይም የአጥቢያው ክርስቲያን ማኅበረ ሰብን የሚጠቅም ተግባር እንዲፈጽም በሥርዐት መሾምን በሚያሳይ ሌላ ሐረግ ወይም ቃል መጠቀም ይችላል።