am_tw/bible/kt/deacon.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ዲያቆን
ዲያቆን ምግብን ወይም ገንዘብን በመሳሰሉ ተግባራዊ ነገሮች አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉትን በመርዳት የሚያገለግል ሰው ነው።
* “ዲያቆን” የሚለው ቃል በቀጥታ የተወሰደው “ባርያ” ወይም “አገልጋይ” የሚል ትርጕም ካለው ግሪክ ቃል ነው።
* የጥንት ክርስቲያኖች ከነበሩበት ዘመን ጀምሮ ዲያቆን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነኛ ድርሻ ያለው የአገልግሎት ዘርፍ ነው።
* ለምሳሌ ከአዲስ ኪዳን እንደምንመለከተው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላሉ መበለቶችና ድኾች ገንዘብና ምግብ በአግባቡ መዳረሱን የሚያጣሩ ዲያቆናት ነበሩ።
* “ዲያቆን” የተሰኘው ቃል፣ “የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ” ወይም፣ “የቤተ ክርስቲያን ሠራተኛ” ተብሎ ሊተረጎም ወይም የአጥቢያው ክርስቲያን ማኅበረ ሰብን የሚጠቅም ተግባር እንዲፈጽም በሥርዐት መሾምን በሚያሳይ ሌላ ሐረግ ወይም ቃል መጠቀም ይችላል።