am_tw/bible/kt/crucify.md

8 lines
954 B
Markdown

# መስቀል (ሰውን)
“መስቀል” ማለት አንድን ሰው መስቀል ላይ ማሰርና በታላቅ ሕመምና ስቃይ እስኪሞት ድረስ እዚያው መተው ማለት ነው።
* የሚሰቀለው ሰው መስቀሉ ላይ ይታሰር ወይም ይቸነከር ነበር። በዚህ መልኩ የሚሰቀሉ ሰዎች በከባድ ደም መፍሰስ ወይም በመታረን ይሞቱ ነበር።
* አደገኛ ወንጀለኞችን ወይም በሮም መንግሥት ላይ ያመፁ ሰዎችን ለመግደል ሮማውያን በእንደዚህ ዐይነቱ ቅጣት ይጠቀሙ ነበር።
* የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ኢየሱስን እንዲሰቅሉ ወታደሮቹ እንዲያዝ ሮማውያን ባለ ሥልጣን ጠየቁ። ወታደሮቹ ኢየሱስን መስቀል ላይ ቸነከሩ። እኢያ ላይ ስድስት ሰዓት ያህል ተሰቃይቶ ሞተ።