am_tw/bible/kt/crucify.md

954 B

መስቀል (ሰውን)

“መስቀል” ማለት አንድን ሰው መስቀል ላይ ማሰርና በታላቅ ሕመምና ስቃይ እስኪሞት ድረስ እዚያው መተው ማለት ነው።

  • የሚሰቀለው ሰው መስቀሉ ላይ ይታሰር ወይም ይቸነከር ነበር። በዚህ መልኩ የሚሰቀሉ ሰዎች በከባድ ደም መፍሰስ ወይም በመታረን ይሞቱ ነበር።
  • አደገኛ ወንጀለኞችን ወይም በሮም መንግሥት ላይ ያመፁ ሰዎችን ለመግደል ሮማውያን በእንደዚህ ዐይነቱ ቅጣት ይጠቀሙ ነበር።
  • የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ኢየሱስን እንዲሰቅሉ ወታደሮቹ እንዲያዝ ሮማውያን ባለ ሥልጣን ጠየቁ። ወታደሮቹ ኢየሱስን መስቀል ላይ ቸነከሩ። እኢያ ላይ ስድስት ሰዓት ያህል ተሰቃይቶ ሞተ።