# መስቀል (ሰውን) “መስቀል” ማለት አንድን ሰው መስቀል ላይ ማሰርና በታላቅ ሕመምና ስቃይ እስኪሞት ድረስ እዚያው መተው ማለት ነው። * የሚሰቀለው ሰው መስቀሉ ላይ ይታሰር ወይም ይቸነከር ነበር። በዚህ መልኩ የሚሰቀሉ ሰዎች በከባድ ደም መፍሰስ ወይም በመታረን ይሞቱ ነበር። * አደገኛ ወንጀለኞችን ወይም በሮም መንግሥት ላይ ያመፁ ሰዎችን ለመግደል ሮማውያን በእንደዚህ ዐይነቱ ቅጣት ይጠቀሙ ነበር። * የአይሁድ ሃይማኖት መሪዎች ኢየሱስን እንዲሰቅሉ ወታደሮቹ እንዲያዝ ሮማውያን ባለ ሥልጣን ጠየቁ። ወታደሮቹ ኢየሱስን መስቀል ላይ ቸነከሩ። እኢያ ላይ ስድስት ሰዓት ያህል ተሰቃይቶ ሞተ።