am_tw/bible/kt/cornerstone.md

967 B

የማእዘን ድንጋይ

“የማእዘን ድንጋይ” የሚለው ሐረግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ተጠርቦ የሕንጻው መሠረት አንድ ጥግ ላይ የሚቀመጥ ትልቅ ድንጋይ ነው።

  • ሌሎች ድንጋዮች ሁሉ የሚለኩትና የሚቀመጡት ከማእዘን ድንጋይ መሠረት ነው።
  • የማእዘን ድንጋይ ሕንፃው በሙሉ ጥንካሬና ዘላቂነት እንዲኖረው በጣም አስፈላጊ ነው።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “የማእዘን ድንጋይ” ሲባል አማኞች ደግሞ ሕያዋን ድንጋዮች ተብለዋል።
  • የማእዘን ድንጋይ ሕንፃውን ደግፎ እንደሚይዝና የሕንፃውን ትክክለኛነት እንደሚወሰን ሁሉ አማኞች የተመሠረቱትና የተደገፉት ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ነው።