# የማእዘን ድንጋይ “የማእዘን ድንጋይ” የሚለው ሐረግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ተጠርቦ የሕንጻው መሠረት አንድ ጥግ ላይ የሚቀመጥ ትልቅ ድንጋይ ነው። * ሌሎች ድንጋዮች ሁሉ የሚለኩትና የሚቀመጡት ከማእዘን ድንጋይ መሠረት ነው። * የማእዘን ድንጋይ ሕንፃው በሙሉ ጥንካሬና ዘላቂነት እንዲኖረው በጣም አስፈላጊ ነው። * አዲስ ኪዳን ውስጥ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “የማእዘን ድንጋይ” ሲባል አማኞች ደግሞ ሕያዋን ድንጋዮች ተብለዋል። * የማእዘን ድንጋይ ሕንፃውን ደግፎ እንደሚይዝና የሕንፃውን ትክክለኛነት እንደሚወሰን ሁሉ አማኞች የተመሠረቱትና የተደገፉት ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ነው።