am_tw/bible/kt/cornerstone.md

9 lines
967 B
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# የማእዘን ድንጋይ
“የማእዘን ድንጋይ” የሚለው ሐረግ ልዩ በሆነ ሁኔታ ተጠርቦ የሕንጻው መሠረት አንድ ጥግ ላይ የሚቀመጥ ትልቅ ድንጋይ ነው።
* ሌሎች ድንጋዮች ሁሉ የሚለኩትና የሚቀመጡት ከማእዘን ድንጋይ መሠረት ነው።
* የማእዘን ድንጋይ ሕንፃው በሙሉ ጥንካሬና ዘላቂነት እንዲኖረው በጣም አስፈላጊ ነው።
* አዲስ ኪዳን ውስጥ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ “የማእዘን ድንጋይ” ሲባል አማኞች ደግሞ ሕያዋን ድንጋዮች ተብለዋል።
* የማእዘን ድንጋይ ሕንፃውን ደግፎ እንደሚይዝና የሕንፃውን ትክክለኛነት እንደሚወሰን ሁሉ አማኞች የተመሠረቱትና የተደገፉት ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ነው።