am_tw/bible/kt/confess.md

10 lines
1.2 KiB
Markdown

# መመስከር፣ ምስክርነት
መመስከር አንድ ነገር እውነት መሆኑን መቀበል ወይም መናገር ማለት ነው። “ምስክርነት” አንድ ነገር እውነት መሆኑን በቃል ወይም በጽሑፍ በዚያም መስማማት ማለት ነው።
* “መመስከር”እግዚአብሔርን በተመለከተ በድፍረት እውነቱን መናገርን ያመለክታል። ኃጢአት መሥራታችንን መቀበልንም ያመለክታል።
* ሰዎች ኃጢአት መሥራታቸውን ሲናዘዙ፣ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
* አማኞች እርስ በርሳቸው ኃጢአታቸውን ሲናዘዙ መንፈሳዊ ፈውስ እንደሚኖር ሐዋርያው ያዕቆብ በመልእክቱ ጽፎአል።
* አንድ ቀን ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ሰዎች ሁሉ እንደሚመሰክሩ ወይም እንደሚናገሩ ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች ጽፎአል።
* ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ካመኑና እግዚአብሔርንም ከሙታን እንዳስነሣው ሰዎች ከመሰከሩ እንደሚድኑ ጳውሎስ ይናገራል።