# መመስከር፣ ምስክርነት መመስከር አንድ ነገር እውነት መሆኑን መቀበል ወይም መናገር ማለት ነው። “ምስክርነት” አንድ ነገር እውነት መሆኑን በቃል ወይም በጽሑፍ በዚያም መስማማት ማለት ነው። * “መመስከር”እግዚአብሔርን በተመለከተ በድፍረት እውነቱን መናገርን ያመለክታል። ኃጢአት መሥራታችንን መቀበልንም ያመለክታል። * ሰዎች ኃጢአት መሥራታቸውን ሲናዘዙ፣ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። * አማኞች እርስ በርሳቸው ኃጢአታቸውን ሲናዘዙ መንፈሳዊ ፈውስ እንደሚኖር ሐዋርያው ያዕቆብ በመልእክቱ ጽፎአል። * አንድ ቀን ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ሰዎች ሁሉ እንደሚመሰክሩ ወይም እንደሚናገሩ ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች ጽፎአል። * ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ካመኑና እግዚአብሔርንም ከሙታን እንዳስነሣው ሰዎች ከመሰከሩ እንደሚድኑ ጳውሎስ ይናገራል።