am_tw/bible/kt/confess.md

1.2 KiB

መመስከር፣ ምስክርነት

መመስከር አንድ ነገር እውነት መሆኑን መቀበል ወይም መናገር ማለት ነው። “ምስክርነት” አንድ ነገር እውነት መሆኑን በቃል ወይም በጽሑፍ በዚያም መስማማት ማለት ነው።

  • “መመስከር”እግዚአብሔርን በተመለከተ በድፍረት እውነቱን መናገርን ያመለክታል። ኃጢአት መሥራታችንን መቀበልንም ያመለክታል።
  • ሰዎች ኃጢአት መሥራታቸውን ሲናዘዙ፣ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚላቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
  • አማኞች እርስ በርሳቸው ኃጢአታቸውን ሲናዘዙ መንፈሳዊ ፈውስ እንደሚኖር ሐዋርያው ያዕቆብ በመልእክቱ ጽፎአል።
  • አንድ ቀን ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ሰዎች ሁሉ እንደሚመሰክሩ ወይም እንደሚናገሩ ሐዋርያው ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች ጽፎአል።
  • ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ካመኑና እግዚአብሔርንም ከሙታን እንዳስነሣው ሰዎች ከመሰከሩ እንደሚድኑ ጳውሎስ ይናገራል።