am_tw/bible/kt/compassion.md

1.0 KiB

ርኅራኄ፣ ርኅሩኅ

“ርኅራኄ” ለሰዎች ማሰብ፣ አተለይም መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች እነርሱ ቦታ ሆኖ ስሜታቸውን መጋራትን ያመለክታል። “ርኅሩኅ” ሰው ለሌሎች ሰዎች ያስባል እነርሱንም ይረዳል።

  • ብዙውን ጊዜ፣ “ርኅራኄ” የሚለው ቃል ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች ጥንቃቄ ማድረግንና እነርሱን ለመርዳት አንዳች ነገር ማድረግንም ይጨምራል።
  • እግዚአብሔር ርኅሩኅ መሆኑን ያም ማለት እርሱ ፍቅርንና ምሕረትን የተሞላ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
  • ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ፣ “ርኅራኄን ልበሱ” በማለት ይመክራቸዋል። ለሰዎች የሚያስቡና የሚጠነቀቁ እንዲሆኑና ችግር ውስጥ ያሉትን ለመርዳት ንቁዎች እንዲሆኑ ያስስባቸዋል።