am_tw/bible/kt/compassion.md

8 lines
1.0 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ርኅራኄ፣ ርኅሩኅ
“ርኅራኄ” ለሰዎች ማሰብ፣ አተለይም መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች እነርሱ ቦታ ሆኖ ስሜታቸውን መጋራትን ያመለክታል። “ርኅሩኅ” ሰው ለሌሎች ሰዎች ያስባል እነርሱንም ይረዳል።
* ብዙውን ጊዜ፣ “ርኅራኄ” የሚለው ቃል ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች ጥንቃቄ ማድረግንና እነርሱን ለመርዳት አንዳች ነገር ማድረግንም ይጨምራል።
* እግዚአብሔር ርኅሩኅ መሆኑን ያም ማለት እርሱ ፍቅርንና ምሕረትን የተሞላ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።
* ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ፣ “ርኅራኄን ልበሱ” በማለት ይመክራቸዋል። ለሰዎች የሚያስቡና የሚጠነቀቁ እንዲሆኑና ችግር ውስጥ ያሉትን ለመርዳት ንቁዎች እንዲሆኑ ያስስባቸዋል።