# ርኅራኄ፣ ርኅሩኅ “ርኅራኄ” ለሰዎች ማሰብ፣ አተለይም መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች እነርሱ ቦታ ሆኖ ስሜታቸውን መጋራትን ያመለክታል። “ርኅሩኅ” ሰው ለሌሎች ሰዎች ያስባል እነርሱንም ይረዳል። * ብዙውን ጊዜ፣ “ርኅራኄ” የሚለው ቃል ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች ጥንቃቄ ማድረግንና እነርሱን ለመርዳት አንዳች ነገር ማድረግንም ይጨምራል። * እግዚአብሔር ርኅሩኅ መሆኑን ያም ማለት እርሱ ፍቅርንና ምሕረትን የተሞላ እንደ ሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። * ጳውሎስ ለቆላስይስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ፣ “ርኅራኄን ልበሱ” በማለት ይመክራቸዋል። ለሰዎች የሚያስቡና የሚጠነቀቁ እንዲሆኑና ችግር ውስጥ ያሉትን ለመርዳት ንቁዎች እንዲሆኑ ያስስባቸዋል።