am_tw/bible/kt/circumcise.md

1.4 KiB

መገረዝ፣ ግዝረት

“መግረዝ” ከወንድ ወይም ወንድ ከሆነ ትንሽ ልጅ ብልት ትርፍ የሆነውን ቆዳ መቊረጥ ማለት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የግርዘት ሥርዓት ሊኖርም ይችላል።

  • ከእነርሱ ጋር ያደረገው ኪዳን ምልክት እንዶን ቤተ ሰብ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድና አገልጋይ እንዲገረዝ እግዚአብሔር አብርሃምን አዝዞት ነበር።
  • ቤተ ሰባቸው ውስጥ የሚወለድ ማንኛውንም ወንድ እንዲገርዙ እግዚአብሔር የአብርሃም ዘሮችንም አዝዞአቸዋል።
  • “የልብ መገረዝ” የሚለው ሐረግ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ከሰው፣ ኃጢአት “መቆረጥን” ወይም፣ “መወገድን” ያመለክታል።
  • በመንፈሳዊ ይዘቱ፣ “የተገረዙ” ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እግዚአብሔር ከኃጢአት ያነጻቸውንና የእርሱ ሕዝብ የሆኑትን ሰዎች ያመለክታል።
  • “ያልተገረዙ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የብልት ሥጋቸው ያልተገረዘ ሰዎችን ነው። ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ በመንፈሳዊ ደረጃ ያልተገረዙትን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የሌላቸውን ያመለክታል።